ያደመቀን መብራት ሲደበዝዝ

ያደመቀን መብራት ሲደበዝዝ መልካችን ምን ይመስላል? (መዝሙር 131፡1- 3) ዳዊት ገና የአባቱን በጎች ሲጠብቅ ሳለ አንበሳና ድብ እየመታ በጎቹን ያስጥል ነበር። ከወንድሞቹም መካከል ተመርጦ ለንግሥና በሳሙኤል ተቀባ ። በሙዚቃ ችሎታ ተወዳዳሪ አልተገኘለትምና ንጉሱን እንዲያፅናና ተጠራ።እስራኤልን የተገዳደረውንና በእግዚአብሄር ስም ላይ የተሳለቀውን ጎልያድን ገድሎ እስራኤልን ታደገ። ሳዖል ሺህ ገደለ ዳዊት እልፍ ገደለ እያሉ ሴቶች እየተቀባበሉ ዘፈኑለት። የእስራኤልን ጭፍራ እየመራ ብዙ ጊዜ ድል …

የማይዋዥቅ ማንነት

የስኬት ደስታ እንደ ወይን ጠጅ ቶሎ ራስ ላይ ይወጣና ሰው መሆናችንን ሊያስረሳን ሲችል ፤ የውድቀት ወይም የአለመሳካት ሃዘን ደግሞ ወደ ልብ ወርዶ ሰው መሆናችንን ሊያስጠላን ይችላል። ሁለቱም ማለትም ስኬትና ውድቀት ህይወታችንን የማመሳቀል አቅማቸውና አደገኛነታቸው እኩል ነው። በምድር ላይ እስካለን ሁለቱም እንድየምክንያቶቻቸው ተራ በተራ ሊፈራረቁብን የግድ ነው ። ስለሆነም ሁለቱንም እንደየአመጣጣቸው ተቋቁመን፤ ሰላማችን ሳይናጋና ነፍሳችንም ሳትታወክ በድል ማለፍ የምንችለው እግዚአብሄር በክርስቶስ …