ከምሪት ይልቅ መሪውን

ያደመቀን መብራት ሲደበዝዝ መልካችን ምን ይመስላል?
(መዝሙር 131፡1- 3)
ዳዊት ገና የአባቱን በጎች ሲጠብቅ ሳለ አንበሳና ድብ እየመታ በጎቹን ያስጥል ነበር። ከወንድሞቹም መካከል ተመርጦ ለንግሥና በሳሙኤል ተቀባ ። በሙዚቃ ችሎታ ተወዳዳሪ አልተገኘለትምና ንጉሱን እንዲያፅናና ተጠራ።እስራኤልን የተገዳደረውንና በእግዚአብሄር ስም ላይ የተሳለቀውን ጎልያድን ገድሎ እስራኤልን ታደገ። ሳዖል ሺህ ገደለ ዳዊት እልፍ ገደለ እያሉ ሴቶች እየተቀባበሉ ዘፈኑለት። የእስራኤልን ጭፍራ እየመራ ብዙ ጊዜ ድል ያደርግ ነበር። በሳዖል ይፈራ ፤ በልጁ በዮናታን እጅግ ይወደድ ነበር። በእስራኤል ሁሉ የተወደደና በሁሉ ፊት ሲገባና ሲወጣ አስተውሎ ያደርግ ነበር።
ከሁሉም በላይ እግዚአብሔር ከርሱ ጋር እንደነበር እርሱ ራሱ ህዝቡና ጠላቶቹ ሁሉ ያውቁ ነበር። ከሳዖል በቀር እስራኤል ሁሉ አይኑን የጣለበትና ልቡ ያረፈበት፤ መልከ መልካም እግዚአብሔርን የሚፈራ ጉብል ወጣት ነበር።
ይህ ዳዊት ልቡ ምን ዓይነት ነበር? ዳዊትም ሲናገር እንዲህ አለ፡- “እግዚአብሔር ሆይ፤ ልቤ አልታበየም፤ ዐይኔ ከፍ ከፍ አላለም፤ ሐሳቤ ለዐጒል ትልቅነት አልተነሣሣም፤ ከዐቅሜም በላይ አልተንጠራራሁም። ” (ቁጥር1)
Read More
የስኬት ደስታ እንደ ወይን ጠጅ ቶሎ ራስ ላይ ይወጣና ሰው መሆናችንን ሊያስረሳን ሲችል ፤ የውድቀት ወይም የአለመሳካት ሃዘን ደግሞ ወደ ልብ ወርዶ ሰው መሆናችንን ሊያስጠላን ይችላል። ሁለቱም ማለትም ስኬትና ውድቀት ህይወታችንን የማመሳቀል አቅማቸውና አደገኛነታቸው እኩል ነው። በምድር ላይ እስካለን ሁለቱም እንድየምክንያቶቻቸው ተራ በተራ ሊፈራረቁብን የግድ ነው ። ስለሆነም ሁለቱንም እንደየአመጣጣቸው ተቋቁመን፤ ሰላማችን ሳይናጋና ነፍሳችንም ሳትታወክ በድል ማለፍ የምንችለው እግዚአብሄር በክርስቶስ ኢየሱስ የሰጠንን ማንነት በትክክል ስንረዳ ብቻ ነው። ንጉስ ዳዊት ከዙፋኑ በተባረረ ጊዜ እንዲህ አለ፦ ” እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ ግን ዙሪዬን የምትከልል ጋሻ ነህ: ክብሬና ራሴንም ቀና የምታደርግ አንተ ነህ።” (መዝ 2፡3) እግዚአብሔርን ” አንተ ክብሬ ነህ” አለው። Read More
ያለምክንያት የሆነ የልብ ሃዘን የለም። ምክንያቱ ቢገባን ባይገባንም ሁሉን አዋቂ በሆነው በእግዚአብሄር ፊት ሃዘናችንን እንደውሃ እናፍስሰው። በፊቱ የፈሰሰን የልባችንን ሃዘን እንደፈቃዱና እንደሃሳቡ ለራሱ ክብር እንዲጠቀም ስንፈቅድለት ከልባችን ሃዘን ትልቅ ነገር ያወጣል። እኛም በማዳኑ ደስ ይለናል። ቀድሞውኑ ዓላማው እኛ ስናዝን ማየት አልነበረም። ደስም አይለውም። ይሁን እንጂ ታዲያ ልባችን መቼ እንዲሁ በዋዛ በፊቱ የሚፈስ ሆነና። ልቧ ያዘነባት ሴት ሐና ህይወቷ የሚያስተምረን ይህንን እውነት ነው። እግዚአብሔር አዋቂ ነው ሀዘናችንንም ለራሱ ክብር እንዴት እንዲጠቀም ያውቃል። ” የእግዚአብሔር የጥበቡና የዕውቁቱ ባለጠግነት እንዴት ጥልቅ ነው! ፍርዱ አይመረመርም: ለመንገዱም ፍለጋ የለውም! ….. ሁሉ ከእርሱ: በእርሱ: ለእርሱ ነውና፣ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን አሜን።” ሮሜ11:36